ወታደራዊ ስልጠና ለላቀ የአመራር ብቃት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የመንግስት አመራሮች ወታደራዊ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ እና የደህንነት ፖሊሲዎችን በአግባቡ እንዲረዱ እያደረገ ነዉ፡፡ አሁን ላይ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ይወስዱ የነበረውን ስልጠና በማጠናቀቅ ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል፡፡ ይህ የአጭር ጊዜ የወታደራዊ ስልጠና ትምህርት በብዙ ሀገራት የፖለቲካ አመራሮች የወታደራዊ ስትራቴጂን ጨምሮ የደህንነት ፖሊሲን በአግባቡ እንዲረዱ የሚደርግ ሥልጠና ነው። ይህን ከሚሰጡ ሀገራት መካከል አሜሪካ፣ ቻይና፣ ዪናይትድ ኪንግደም እና ሕንድ ተጠቃሾች ሲሆኑ እንደ እስራኤል፣ ስዊዘርላንድ እና ሰሜን ኮሪያ ያሉ ሀገራት ደግሞ ፖለቲከኞቻቸው የወታደራዊ ልምድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ አሰራርን ይከተላሉ፡፡ ኢትዮጵያም ይህን ልምድ በመውሰድ ለከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችዋ ስልጠናዎችን እየሰጠች ነው፡፡ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ስልጠናውን ወስደው አጠናቀው ወደ ስራቸው ተመልሰዋል ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የስልጠናውን መጠናቀቅ ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የወታደራዊ ሳይንስ ሥልጠናው በአካላዊ፣ በአእምሯዊና በተግባር ዝግጁነት ረገድ አዲስ አቅም ያስጨበጠ ነው ብለዋል፡፡ የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠናው ለሲቪል አመራሮቹ መሰጠቱ ስለ ወታደራዊ አስተሳሰብ፣ ስለ መከላከያ ሥርዓት፣ ስለ ሀገራዊ ደህንነት እና ስ…