የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችን አዘጋጅተው ሕዝብን በብቃት ማገልገል አለባቸው – ቤኔዲክታ ላሲ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችን አዘጋጅተው ሕዝብን በብቃት ማገልገል አለባቸው አሉ የአፍሪካ የአስተዳደር ማዕከል ሊቀመንበር ቤኔዲክታ ላሲ፡፡ 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ “እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ቤኔዲክታ ላሲ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን ለመያዝ ከማቀድ ባለፈ ሀገራቸውን በብቃት ለመምራት፣ የረጅም ጊዜ የልማት አቅጣጫ ለመቅረጽና የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማሳካት ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት መዘጋጀት አለባቸው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተልዕኮ ሥልጣን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችን አዘጋጅተው ሕዝብን በብቃት ማገልገል መሆኑን አስገንዝበዋል። ፓርቲዎች መሪዎችን ከማፍራት ባለፈ የመንግሥት አስተዳደርን፣ የሀገር ኢኮኖሚንና የተለያዩ የልማት ዘርፎችን ለመምራት የሚያስችሉ ዕውቀትና አቅም በቅድሚያ ሊገነቡ ይገባል ብለዋል፡፡ ሀገራዊ ተቋማት ለመሪዎች የሚሰጡት የአራትና የአምስት ዓመት የሥልጣን ዘመን ቢኖርም የኢንዱስትሪ መሠረትን መገንባት፣ የኃይል ሥርዓትን ማስፋፋትና የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ የረጅም ጊዜ ተከታታይ ሥራ እንደሚጠይቅ አመልክተዋል። በፖለቲካዊ ሽግግር ምክንያት ቀጣይነት ያላቸው የልማት ሥራ…