08-11-2026

EthiopiaFana BC

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። ‎በውይይታቸውም በአህጉራዊ አስተዳደር፣ አካታች የፖለቲካ ሂደቶች፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ የልማት ጉዳዮች እንዲሁም የአፍሪካን አመራር በማጠናከር ዙሪያ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። The post ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Media Corporation S.C.

ተጨማሪ ርዕሰ ዜናዎች