08-11-2026

EthiopiaFana BC

የመደመር መንግሥት ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ብልጽግና እየሠራ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የመደመር መንግሥት ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ብልጽግና እየሠራ ነው አሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡ 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ “እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአባላትና የአደረጃጀት ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ ያላቸውን አቅም ወደ ጠንካራ ተቋማዊ ብቃት በመቀየር በሕዝብ ኑሮ ላይ በሚያመጡት ተጨባጭ ለውጥ መመዘን አለባቸው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳብ የሚያፈልቁ፣ መሪዎችን የሚያፈሩና ከምርጫ ውድድር በኋላም የልማት ሥራዎችን የሚያስቀጥሉ ተቋማት መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል። የብልጽግና ፓርቲ በመደመር ፍልስፍና የተለያዩ ሰዎችን፣ ተቋማትንና አቅሞችን በጋራ ዓላማ ዙሪያ በማሰባሰብ ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ብልጽግና እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል። ፓርቲው ከተለያዩ ክልላዊ መሠረቶች የመጡ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ አንድ ሀገራዊ ፓርቲ በማምጣት የጋራ ዜግነትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ፓርቲው ከ16 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ አባላትና በመላ ሀገሪቱ የተዘረጉ መዋቅሮች እንዳሉት ጠቅሰ…

ተጨማሪ ርዕሰ ዜናዎች