08-11-2026

EthiopiaFana BC

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የፊት ገፅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ከገነቡ አምስት ሀገራት አንዷ መሆኗን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በፊት ገፆቻቸው እየዘገቡ ነው፡፡ የመደመር መንግሥት ሀገራዊ ምጣኔ ሀብትን ለማሳደግ፣ መዋቅራዊ ስብራቶችን ለመጠገንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ መንግሥት የተከተለው የኢኮኖሚ መንገድ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በዋናነት በአምስት የምጣኔ ሀብት ምሰሶዎች ማለትም በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ወይም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ነው። በእነዚህ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ እንድትገነባ አስችሏታል፡፡ ይህን የኢኮኖሚ እድገት በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችን እና ቁጥራዊ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ግዙፍ የኢኮኖሚ ግንባታ መገናኛ ብዙሃን በፊት ገፆቻቸው ሽፋን ሰጥተውታል፡፡ የቢዝነስ መፅሔት የሆነው ብሉምበርግ እንደዘገበው÷ በፈረንጆቹ 2025/26 ሐምሌ ወር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 210 ነጥብ 7 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን አስነብቧል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች አንዷ መሆኗን የዘገበው ብሉምበርግ÷ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ…

ተጨማሪ ርዕሰ ዜናዎች