ዓርብ, 6 ኖቬምበር 2026

EthiopiaFana BC

ከራስ አልፎ ለዓለም ገበያ፤ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ስኬትና የምግብ ሉዓላዊነት ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የምግብ ሉዓላዊነትን በተግባር እያረጋገጠች የምትገኘው ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያሳየች የምትገኘው ስኬት የሀገሪቱን የልማት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል። ለረጅም ዘመናት ኢትዮጵያ በስንዴ ፍላጎቷና በሀገር ውስጥ ምርቷ መካከል የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ከውጭ ሀገራት ስንዴ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማውጣት ትገደድ ነበር። ይህም በሀገሪቱ የንግድ ሚዛን ላይ ጫና በመፍጠር ለፈተናዎች ተጋላጭ እንድትሆን ያደርጋት ነበር። ይህንን ተግዳሮት ወደ ዕድል ለመቀየርም ከዓመታት በፊት የመደመር መንግሥት የለውጥ አቅጣጫ በመቀየስ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ ጀመረ። በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የሆነው የስንዴ ልማት የሀገሪቱን የስንዴ ምርት አቅም ከፍ በማድረግ በዘርፉ አዲስ የስኬት ታሪክ እንዲጻፍ አስችሏል። ከዚህ ሥራ ፍሬዎች መካከል በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የጎበኙት የክረምት ስንዴ እርሻ አፈጻጸም አንዱ ነው። ይህ አዲስ አቅጣጫ በመስኖ ቴክኖሎጂ፣ በተሻሻሉ የስንዴ ዘሮች፣ በማዳበሪያ፣ በዘመናዊ የእርሻ ማሽነሪዎችና በተሻለ የአመራረት ሥርዓት የታገዘ ሲሆን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ አርሶ አደሮችን በልማቱ ቀጥታ ተሳታፊ አድርጓል። ይህም የመሬትን ምርታማነት ከማሳደጉ ባሻገር የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ፣ የሥራ…

ተጨማሪ ርዕሰ ዜናዎች