ዓርብ, 6 ኖቬምበር 2026

EthiopiaFana BC

የግብፅ እና የሱዳን “2+2”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብፅ እና የሱዳን “2+2” እሚሉት አንድ የጋራ የውይይት መድረክ አላቸው፤ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ (መስኖ) ሚኒስትሮች በጋራ የሚሳተፉበት ‘’የዲፕሎማሲ እና የቴክኒክ’’ ስብሰባ ነው። የጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ወታደራዊ አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ማሂ ኤል ዲን ሳሌም በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የመልማት መብት በተፃረረ ሁኔታ “የግብፅን የውሃ መብት ከግብፆች ቀድመን እኛ እንጠብቃለን” ማለታቸው የሱዳን ባለሥልጣናት ሱዳንን ምን ያህል ለግብጽ ተላላኪ ለማድረግ እንደሚሠሩ የሚያሳብቅ ነው። የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ ከሁሉም በላይ የራሱን ሕዝብ ከጦርነትና ሰብዓዊ ቀውስ መታደግ ሲገባው፤ ዛሬም ጊዜ ያለፈባቸውን እና ፍትሃዊነት የጎደላቸውን የ1929 እና የ1959 ስምምነቶች በመጥቀስ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ‘’ግብጽን አስቀድሜ እታደጋታለሁ’’ ማለቱ፣ ግብፅም ‘’የሱዳንን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ እና የውሃ መብቷን ለማስከበር አስፈላጊውን ርምጃ ሁሉ ለመውሰድ ዝግጁቷን መግለጿ፣ የሁለቱን ሀገሮች ሕዝቦች የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም አይደለም። በርግጥ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “የግብፅን ውሃ ከእነሱ ቀድመን እንጠብቃለን” ማለታቸው፣ ሱዳን አሁን ባለችበት የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በግብፅ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሥር ሙሉ በሙሉ መውደቋ…

ተጨማሪ ርዕሰ ዜናዎች