አዲስ አበባ፡ የአፍሪካ የጋራ ርዕይ፣ የትብብርና የልማት መድረክ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ በጋራ ስትቆም ትጠነክራለች፤ በጋራ ስትሠራ ታድጋለች፤ በጋራ ስትወስን የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን ትቀርፃለች። አዲስ አበባ የአፍሪካ የጋራ ቤት ብትሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አህጉራዊ መድረኮች በብዛት የሚስተናገዱባት አልነበረችም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የከተማዋ መሰረተ ልማቶች እጥረትና አለመዘመን ብሎም ምቹ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ያለመፈጠራቸው ነው። ይህን ጉድለት ለመሙላትና በሁሉም መስክ አዲስ አበባን የስበት ማዕከል ለማድረግ በጥቂት ዓመታት የተሰራው ስራ ዛሬ በርካታ ውጤቶችን እያስመለከተን ይገኛል። በአጭር ጊዜ በከተማዋ የተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማቶችና የዘመኑ አገልግሎት መስጫዎች ከተማዋን ተመራጭ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል አድርጓታል። አዲስ አበባ አሁን በመቶዎች ብቻ ሳይሆን በአስር ሺዎች ተሳታፊ የሚገኙባቸውን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች ለማስተናገድ የሚያስችል አስተማማኝ አቅም ፈጥራለች፤ ስብሰባዎቹንም እያስተናገደች ትገኛለች። በዚህ ሳምንትም አንድ ወሳኝ አህጉራዊ ጉባኤ በከተማዋ ይስተናገዳል። ይሄውም የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ “ለዕድገት መምራት፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ የወደፊት እጣ ፈንታ ቀያሾች ሆነው(Governing for Growth: Political Parties as Architects of Africa’s Economic Future…