የዓለማችን እጅግ ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሽግግር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው – ብሉምበርግ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት እያከናወነችው የሚገኘው ቁርጠኝነት የተሞላበት የኤሌክትሪክ ተሸካርካሪዎች አብዮት ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል፡፡ ታዋቂው የዜና አውታር ብሉምበርግ ለዕይታ ባበቃው ሰፊ ዘገባ፥ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለየት ያሉና ድፍረት የተሞላባቸው ርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረግ ትታወቃለች ብሏል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በካርቦን ልቀትና በነዳጅ ጥገኝነት ሳቢያ የሚታዩ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ፣ በርካታ የበለጸጉ ሀገራት እንኳን ያልደፈሩትን ቁርጠኛ ርምጃ በመውሰድ የዓለምን ትኩረት በመሳብ ላይ እንደምትገኝ ብሉምበርግ አትቷል። በፈረንጆቹ 2024 ወዲህ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በማገድ፤ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመሸጋገር ታሪካዊ ውሳኔ ማሳለፏን አስታውሷል። ይህ ውሳኔ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጥንካሬ የሚያረጋግጥና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ታላቅ ድል ነው። ኢትዮጵያ በየዓመቱ እስከ 5 ቢሊየን ዶላር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለነዳጅ ግዢ ወጪ ስታደርግ መቆየቷን የጠቀሰው ዘገባው፤ ይህ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ጫና ለመቀነስና የኢኮኖሚ አቅምን ለማጠናከር ወሳኝ ነው ብሏል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት የሀገሪቱን የፋይናንስ አቅም በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያ…