ዓርብ, 6 ኖቬምበር 2026
📺 Ethiopia · የቀጥታ ቴሌቪዥን
ቀጥታ
ቀጥታ ዜና ይመልከቱAfricanews

የቅርብ ጊዜ የEthiopia ዜናዎች

Fana BC

አብዛኛው የውኃ ድርሻ ለግብጽ ብቻ እንዲሄድ መደረጉ ህሊና ያለው ሰው የሚቀበለው አይደለም – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አብዛኛው የውኃ ድርሻ ለግብጽ እንዲሄድ መደረጉ ህሊና ያለው ሰው የሚቀበለው አይደለም አሉ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር):: የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳነሱት፤ የሱዳን ወገኖችና ምሁራን ሊገነዘቡት የሚገባው ነባሩ የቅኝ ግዛት ውል ሱዳኖችንም ጭምር አስሮ ያስቀመጠ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ስታድግ ብቻዋን እንዳልሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ የምታድገው ቀጣናውን ይዛ ለመነሳት እንደሆነ አመልክተዋል። የውኃው አጠቃቀም ፍትሃዊ እንዳልሆነ እና አብዛኛው ድርሻ ለግብጽ እንዲሄድ መደረጉ ህሊና ያለው ሰው የሚቀበለው አለመሆኑን አንስተዋል፡፡ ግብጾች የኢትዮጵያን የዕድገት ፍጥነት እንደሚፈሩት በመግለጽ ኢትዮጵያ ለእድገት በምታደርገው…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →
Fana BC

ከራስ አልፎ ለዓለም ገበያ፤ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ስኬትና የምግብ ሉዓላዊነት ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የምግብ ሉዓላዊነትን በተግባር እያረጋገጠች የምትገኘው ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያሳየች የምትገኘው ስኬት የሀገሪቱን የልማት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል። ለረጅም ዘመናት ኢትዮጵያ በስንዴ ፍላጎቷና በሀገር ውስጥ ምርቷ መካከል የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ከውጭ ሀገራት ስንዴ ለማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማውጣት ትገደድ ነበር። ይህም በሀገሪቱ የንግድ ሚዛን ላይ ጫና በመፍጠር ለፈተናዎች ተጋላጭ እንድትሆን ያደርጋት ነበር። ይህንን ተግዳሮት ወደ ዕድል ለመቀየርም ከዓመታት በፊት የመደመር መንግሥት የለውጥ አቅጣጫ በመቀየስ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ ጀመረ። በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የሆነው የስንዴ ልማት የሀገሪቱን የስንዴ ምርት አቅም ከፍ በማድ…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →
Fana BC

የግብፅ እና የሱዳን “2+2”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብፅ እና የሱዳን “2+2” እሚሉት አንድ የጋራ የውይይት መድረክ አላቸው፤ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የውሃ (መስኖ) ሚኒስትሮች በጋራ የሚሳተፉበት ‘’የዲፕሎማሲ እና የቴክኒክ’’ ስብሰባ ነው። የጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ወታደራዊ አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ማሂ ኤል ዲን ሳሌም በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የመልማት መብት በተፃረረ ሁኔታ “የግብፅን የውሃ መብት ከግብፆች ቀድመን እኛ እንጠብቃለን” ማለታቸው የሱዳን ባለሥልጣናት ሱዳንን ምን ያህል ለግብጽ ተላላኪ ለማድረግ እንደሚሠሩ የሚያሳብቅ ነው። የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ ከሁሉም በላይ የራሱን ሕዝብ ከጦርነትና ሰብዓዊ ቀውስ መታደግ ሲገባው፤ ዛሬም ጊዜ ያለፈባቸውን እና ፍትሃዊነት የጎደላቸውን የ192…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →
Fana BC

በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው አሉ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)። ሚኒስትሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳነሱት፤ ኢትዮጵያ ግድቦችን እንዳትሰራ የማድረግ ሥራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። ይህ ሥራቸው ኢትዮጵያን ይበልጥ አንድ እንዳደረገ ገልጸው አንድ ከመሆንም አልፎ በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ማንም ሳያግዛት በራሷ አቅም የገነባችው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም ከቻሉ ምን ያህል ማሸነፍ እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። የውሀ ሀብታችንን እንዳናለማ የሚደረጉ ጫናዎችና ሴራዎች ኢትዮጵያውያንን ይበልጥ አንድ እንዲሆኑ እና በጋራ እንዲቆሙ እንዳደረጋቸው አመላክተዋል…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →
Fana BC

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋን ጋር ተወያይተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የአፍሪካ ጉዳዮች የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ዙሪያም ሐሳብ መክረዋል። ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ላይ ለልዩ መልዕክተኛው ገለጻ አድርገዋል፡፡ ሊዩ ሺያንፋ፤ በበኩላቸው ሀገራቸው በአፍሪካ ሰላምና ደህንነትን እንዲሰፍን የሚኖራትን በጎ ሚና እና የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። The post ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛን ጋር ተ…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →
Fana BC

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደረጉ ድጋፎች ይጠናከራሉ – የዓለም ባንክ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ባንክ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳወቀ። የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በጽህፈት ቤታቸው የዓለም ባንክ ተወካዮችን ተቀብለው አነጋግረዋል። ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር የምትሰራቸው ሥራዎች ውጤታማ ናቸው። በዋን ዋሽ ፕሮግራም አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆን ውጤታማ ሥራ ሰርተናል ያሉት ሚኒስትሩ ይህም ውጤት በመንግሥት ጠንካራ ክትትል የመጣ ነው ብለዋል። የዓለም ባንክ ተወካዮች ቡድን መሪ ጁሊያን ቪክተር በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ መንግሥትና በል…

ሙሉውን ዜና ለማንበብ ጠቅ ያድርጉ →